መነሻ ገፅ

እንኳን ደህና መጡ!


 

የክርስቶስ ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን በፈረንጆች አቆጣጠር በ1992 ዓ.ም በሙኒክ ከተማ በስደት በመጡ ሁለት ወንድሞች የስደተኞች ካንፕ በሆነው በአንድ ኮንቴነር ውስጥ በህብረት ደረጃ ተመሰረተች። እግዚአብሔርም ነፍሳትን እየጨመረ ስለመጣ ከህብረት ወደ ቤተ ክርስቲያን ደረጃ ተሸጋገረች። የቤተ ክርስቲያኒቱ ተልእኮ ነጻ የሚያወጣውን ወንጌል በመስበክ ሰዎች ወንጌልን ሰምተው እንዲድኑ ማድረግ፣ የዳኑትን የእግዚአብሔን ቃል በማስተማርና ደቀመዛሙርት በማድረግ ለአገልግሎት ማብቃት እንዲሁም የአገልግሎቷ ግብ የሆነውን ቅዱሳንን ወደ ክርስቶስ ሙላት ልክ እስኪደረሱ ድረስ ማስታጠቅና ማሳደግ ሲሆን እግዚአብሔር ጸጋውን ባበዛለት ልክ ወደ ግቧ እየገሰገሰች ትገኛለች።

ቤተ ክርስቲያኒቱ ከእግዚአብሔር የተቀበለችው ራዕይ ያለ ሲሆን ይህም ራዕይ በሐዋርያት ስራ 1 ፥8 ላይ “ ነገር ግን መንፈስ ቅዱስ በእናንተ ላይ በወረደ ጊዜ ኃይልን ትቀበላላችሁ፥ በኢየሩሳሌምም በይሁዳም ሁሉ በሰማርያም እስከ ምድር ዳርም ድረስ ምስክሮቼ ትሆናላችሁ” አለ።

ጌታችንና መድሓኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ባዘዘው መሰርት ወንጌልን ለሐበሾች፣ለምትገኝብት ምድር ህዝብ በማብሰርና በመመስከር በእንቅስቃሴ ላይ የምትገኝ ሲሆን መጭውን ትውልድ በወንጌል በማስታጠቅ ተረካቢ ለመሆን እንዲጀጋጅና እንዲረከብ እንዲሁም የወንጌል ሌላው ክፍል የሆነውን የረድኤት አገልግሎት በኢትዮጵያና በኤርትራ በማገልገል ላይ ትገኛልች።

ቤተ ክርስቲያኒቱ ከእግዚአብሔር ባለጠግነት የተነሳ የራሷ ማምለኪያ ስፍራ ገዝታ ከ 2014 ዓ.ም ጀምሮ በዚሁ የማምለኪያ ስፍራ እግዚአብሔርን በማምለክ ላይ ትገኛለች።


live-stream-am

 

  • ስብከቶች
  • መጽሐፍ ቅዱስ ጥናት
  • ፕሮግራሞች
  • አድራሻ

 

 

 

 


Comments are closed.